የፉክክር ስሜት
በቢሮ አካባቢ የሚሆን ውስጣዊ ፉክክር ለድርጅቶች ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ሰዎች በርትተው እንዲሠሩና ሰፋ አድርገው እንዲያስቡም ያአርጋቸዋል። ሆኖም ግን አንዳንድ ጊዜ ውድድር ወይም ፉክክር ጤናማ ወደ አልሆነ አቅጣጫ ሊወሰድም ይችላል። ሰዎች እርስ በእርሳቸው ሊቃረኑ፥ ስለ ሥራቸው ዋስትና ሊፈሩ ና መላ ሕይወታችው ላይ ተጽእኖ እስከሚያመጣ ሊዘልቅ ይችላል። እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ ሰዎች ከሌላው ሁሉ በልጠው ለመታየት እንዲያስቡ ሊመራቸው ወይም አንዱ ሌላውን ወደ ታች እንዲስብ ሊያደርጋቸው ይችላል። ይህም አንዱ አንዱን ከበስተኋላ መውጋት ቡድናዊ መሆንና ሌላውን ማጥቃት ሊያመጣ ይችላል።
ታዲያ ምን እናድርግ? በአመራር ላይ ያላችሁ ሁኑ ወይም የበታች ሠራተና ከሌሎች ጋር አብሮ መሥራትን አበረታቱ፤ ከሥራ ጓደኛችሁ ጋር ጤናማ የሆነ ውይይት ለማድረግ ራሳችሁን ክፍት አድርጉ፤ ይህም ለሰውነታችሁ ሆነ ለአእምሮአችሁ ጤናማ የሆነ እርምጃ ነው። ይህን በማድረጋችሁ ውጤታማ ትሆናላችሁ አዎንታዊና ጤናማ በሆነ መንገድም ዕድገት ከፍ ወዳለ ደረጃ ልትደርሱ ትችላላችሁ።
ምንጭ beliefnet
ምንጭ beliefnet
No comments:
Post a Comment