Monday, November 4, 2013

« ትህትና» የቃሉ ትርጉም

« ትህትና» ወይም « ራስን ማዋረድ» የባሪያ ባሕርይ ወይም ሥነ ምግባር እንጂ የኵሩዎቹ የሮም ዜጎች ባሕርይ ተደርጎ አይታሰብም ነበር። በዚህም የጥንታዊት ግሪክ የሞራል ሊቃውንት « ትህትና» የዝቅተኛ መደብ ኅብረተሰብ ባሕርይ እንደሆነ አድርገው ይናገሩ ነበር።  « ትሕትና» የሚለው ቃል ተትሕተ፥ ተዋረደ፥ ዝቅ አለ፥ ወደታች አለ የሚል ነው። ለዚህ ቃል ምንጭ የሆነው የግሪኩ ሥረወ ቃል « ታፔይኖ የሚለው ቃል ነው። ትርጉሙ  « ተራራ መደልደል» ማለት ነው። ይህም ክርስቲያናዊ የሆነን ትሕትና ትክክለኛ ትርጉም ያመለክተናል። ይህም ከፍ ያለ ሰው ራሱን ዝቅ ለማድረግ መወሰን ክብርን ማንነትን መተውን የሚያመለክት ነው። በመሆኑም ትሕትና ለራስ አክብሮትን የማጣት በሽታና የዝቅተኝነት ስሜት መገለጫ ሳይሆን ሌሎችን ለማገልገልና እነርሱን ለመጥቀም ቦታን መተው የሚያመለክት ነው።ይኸውም ሊታወቅ ራሱ ክርስቶስ ከፍ ካሉት ከፍ ያለ የእግዚአብሔር ልጅ ሲሆን ትሑት ሆኖ ራሱን አዋርዶ ሌሎችን አገልግሎአል። ( ማቴዎስ 11፥29) 

No comments:

Post a Comment