Read in PDF
ምዕራፍ ፳፩፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ የሰማያዊው የአብ ልጅ እንድሆን አድርገኝ፤ አማኑኤል ሆይ ከአንተ ጋር አዋሕደኝ። አንተ ከዓለም አስቀድሞ የነበርህ ነህ። . . .
ምዕራፍ ፳፩፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ የሰማያዊው የአብ ልጅ እንድሆን አድርገኝ፤ አማኑኤል ሆይ ከአንተ ጋር አዋሕደኝ። አንተ ከዓለም አስቀድሞ የነበርህ ነህ። . . .
ምዕራፍ ፳፪፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ በእርሷ እነጻ ዘንድ ቅዱስ ስምህም በልቡናዬ ውስጥ ይታተም ዘንድ፥ አምላካዊት በሆነች እሳት እጠበኝ። ስምህ የሕይወት ውኃ ምንጭ ነውና፤ ስምህ በውስጡ የታተመበት የሕይወት ውኃን ያፈልቃልና፤
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ለዓለም ሁሉ ሕይወትን የምትሰጥ የሕይወት ኅብስት ነህ። በአንተ በሕይወት እኖር ዘንድ፥ የሕይወትን ኅብስት ስጠኝ።
ምዕራፍ ፳፫፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ የሰማዩን መንግሥት ፈልጉ ሌላው ሁሉ ይጨመርላችኋል ያልክ፥ አንተ መንግሥትም ሕይወትም ነህ። የሰማዩን መንግሥትና የዘላለምን ሕይወት አገኝ ዘንድ ስጠኝ።
ምዕራፍ ፳፬፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ አምላካዊት በሆነች እሳትህ አቃጥለኝ፤ ይህችን እሳትበሕሊናዬ ውስጥም አቀጣጥላት፤ ስለእርሷም « እሳትን በምድር ላይ ልጥል መጣኹ፤ እንድትቀጣጠልም እወዳለሁ» ያልህ፤ ክፋትን የሚያበቅሉ እሾሆችን ሁሉ ታቃጥል ዘንድ በኅሊናዬ ውስጥ አንድዳት።
No comments:
Post a Comment