ምዕራፍ ፲፯፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ከእንቅፋት ደንጋይና ከኑፋቄ ጦር አድነኝ። የክብርህን ውበት ይመለከቱ ዘንድ አእምሮዬንና ልቡናዬን አንድ አድርግልኝ። ዳግመኛም ከውድቀት ቅድስት በምትሆን ትንሣኤህ አድነኝ። አንተ የሕይወት ትንሣኤ ነህና። ያንተን አምላክነት የሚጠራጠር፥ በዘላለም ውድቀት ውስጥ ይወድቃልናል። በአንተ በአምላክነትህ የሚታመን ደግሞ ሕይወት በተመላች፥ ሞትና ውድቀት በሌላት ትንሣኤ በክብርህ ይነሣል።ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ቅድስት በምትሆን ትንሣኤህ አስነሣኝ። እንወደድከው እንደፈቃድህም መግበኝ።
ምዕራፍ ፲፰፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ሥጋዊ በሚሆን አካል (በየጥቂቱ) ያደግህ፥ ለአንተ ቅድስተ ቅዱሳን እሆን ዘንድ፥አምላካዊት የሆነች አእምሮ ትጨምርልኝ ዘንድ፥ መንፈሳዊት በሆነች መታነጽ ታንጸኝና ታሳድገኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።
ምዕራፍ ፲፰፤ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ሥጋዊ በሚሆን አካል (በየጥቂቱ) ያደግህ፥ ለአንተ ቅድስተ ቅዱሳን እሆን ዘንድ፥አምላካዊት የሆነች አእምሮ ትጨምርልኝ ዘንድ፥ መንፈሳዊት በሆነች መታነጽ ታንጸኝና ታሳድገኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።
Thank you Kesis!! Kalehiwot yasemalin!!!
ReplyDelete