READ In PDF
ምዕራፍ ፲፬፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ በኃጢአት የሞተችውን ነፍሴን ፈውሳት፤ ስምህን ለማመስገንም አንቃት።
ምዕራፍ ፲፭፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ አርባኛው ቀን በተፈጸመ ወት አንተ የቅዱሳን ቅዱስ ስትሆን፥ ቁርባናትን ያመጡ ዘንድ ሙሴን ያዘዝከው አንተ ስትሆን፥ በእጁ የሰጠኸውን ሕግ ትፈጽም ዘንድ አርባኛው ቀን በተፈጸመ ወቅት ወደ ቤተ መቅደስ የመጣህ፥ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ልቤ መቅደስህ ይሆን ዘንድ አድርገው፥ ሕሊናዬም በፊትህ ተቀባይነት ያለው ቁርባን እንዲሆን አድርገው። አንተ ተቀባይነት ያለው ቍርባን፥ ከአባትህና ከመንፈስ ቅዱስም ጋር ቍርባንን የምትቀበል ነህና።
ምዕራፍ ፲፮፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ስምዖን በክንዱ የተሸከመህና ወደ ቤተ መቅደስ ያስገባህ፥ልቤና ሕሊናዬ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይሸከሙህ፥ በዚያም ታላቁን ብርሃንህን ይመልከቱ።ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ከዚህ ኃላፊ ከሆነው ዓለም እስራት ነጻ እንድታወጣው ስምዖን እንደለመነህ፥ ልመናውንም እንደፈጸምክለት፥ የእኔንም ልመና ፈጽምልኝ፤ ከዚህ ከንቱ ከሆነው ዓለም እስራትም ፍታኝ።ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ስምዖንን ከዚህ አለም ፍላጎት ነፃ እንዳደረግኸው፥ እንዲሁ የእኔንም ልቡናና ሕሊናዬን ከዚህ ፈራሽ ከሆነው ዓለም ቀንበር ፍታው።

No comments:
Post a Comment