Wednesday, December 19, 2012

ወር አበባና ቅዱስ ቍርባን በተአምረ ሥላሴ

የእብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተአምራታቸው ይህ ነው። በረከታቸው ከእኛ ጋር ይሁን አሜን። 

በአንዲት ዕለት ብዙ ሰዎች ቍርባን ለመቀበል ወደ ወደቤተ ክርስቲያን ሄዱ። ነገር ግን የተቀበሉ ቢመስላቸውም የእግዚእብሔር መላእክት ይከለክሉአቸው ነበር። በዚያች አገር ግን፥ በወር አባባዋ ጊዜ የነበረች አንዲት ሴት ነበረች፥ « ዛሬ በክፉ ምግባሬ ከወንድሞቼ ጋር ቅዱስ ቁርባን እንዳልቀበል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ለዩኝ»  እያለች ታዝን ነበር። ነገር ግን መላእክት ከህዝቡ የወሰዱትን ለዚህች በወር አበባ ላለች ሴት ሲያቀብሉአት አረጋዊ የሆነ አንድ መነኩሴ ተመለከተና በመደነቅ ለሀገሩ ሁሉ ተናገረ። የሰሙት ሕዝብ ሁሉ ስለተደረገው ስለዚህ ነገር እጅግ አደነቁ። ይህም የሆነው በወርኃ ታኅሣሥ ነው።

ምንጭ፡ ዜና ሥላሴ የተባለው የቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍ። 

10 comments:

 1. Yihinin Leyteh Post madregih Mindin New ?
  Min LeMalet Felgeh New ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንዳንድ ጊዜ ፖስት የምናደርጋቸው ነገሮች ውይይት እንዲፈጥሩ፥ ጤናማ በሆነ መንገድ ራሳችንን እንድንመረምር የሚያደርጉ ነገሮች ናቸው። ይህንን ፖስት አደርግኁ እንጂ በዚህ ዙሪያ የተጻፉ ብዙ ታሪኮች አሉ። (ለምሳሌ በተአምረ ማርያም ያለው።) መንፈሳዊ መልእክቱ ምንድነው ለሚለው፥ እንኳን በተፈጥሮ ግዳጅ (በወር አበባ) ቀርቶ፥ በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን እንኳ እግዚአብሔር ለእኛ የማይለወጥ ፍቅር እንዳለው ለማመልከት ነው። ብዙ እህቶች በዚህ ወቅት ከሚሰማቸው አካላዊ ለውጥ (hormonal change) ባሻገር አንዳንድ ጊዜ ሲያጨንቃቸው የማየው፥ ርኩስ ነኝ እግዚአብሔር ርቆኛል የሚለው ሐሳባቸው ነው። ይህን ተአምር በአጋጣሚ ያገኘሁት « ዜና ሥላሴ» ወይም « ዜና ነገሮሙ» አንዳንድ ጊዜም « ሰይፈ ሥላሴ» ተብሎ የሚጠራው መጽሐፍ ከጥንታውያን የብራና መጻሕፍት ላይ ድንገት ስላገኘኹት ነው። ለኦርቶዶክሳውያን እህቶቼ እግዚአብሔር በረድኤት በፈውስ ሁል ጊዜ የማይለያቸው አምላክ እንደሆነ የሚያመለክት ተአምር ነው ብዬ አስባለሁ። ስለ ጥያቄዎ እግዚአብሔር ያክብርልኝ።

   Delete
 2. Thank you for sharing. Kessis but for the clearity, I would like to compare both realgon view on this topic
  The Bible and the Quran agree: Stay away from menstruating women

  "But if a man be just, and do that which is lawful and right, and hath not ... come near to a menstruous woman.... Ezekiel 18:5"
  They question thee (O Muhammad) concerning menstruation. Say: It is an illness, so let women alone at such times.... Quran 2:222
  a topic upon which Muslims, Christians, and Jews can fully agree! Women are unclean when menstruating and men should stay away from them. Here's what the Bible has to say. (A women who is menstruating is unclean and should be kept away from everyone else for seven days. Whatever she touches or sits on is unclean. Whoever touches a such a women is unclean. Whoever touches her bed is unclean. Whoever touches anything that she sits on is unclean. And anyone who has sex with a menstruating woman is reallyunclean -- unclean for seven days.) Liveticuys 15:19-24... And it goes on and on, but I think you get the point ..... In other places, the Bible refers to menstruation in ways that show how God sees it. Let it not displease my lord that I cannot rise up before thee: for the custom of women is upon me. Genesis 31:34-35 Thou shalt cast them away as a menstruous cloth. Isaiah 30:22 Jerusalem is as a menstrous woman. Lamentations 1:17 They humbled her that was set apart for pollution. Ezekiel 22:10. Now most people argew about this topic. When you read Leviticus 15:19-29 ..And if Matthew 5:17-19 (New Testaments) is really Jesus' words, then; menstruating women cannot "ATTEND CHURCH." If she cannot "ATTEND CHURCH" , then she cannot "RECEIVE COMMUNION inside. Please explain this according to orthodox teaching and if now is okay to attend church and take communion why isn't every orthodox church does the same ?. Thank you.

  ReplyDelete
 3. የተወደዱ ጠያቂዬ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። ጥያቄዎትን ለመመለስ የምሞክረው ከመጨረሻው ነው። ይህን ተአምር በዚህ በጡመራ መድረክ ላይ ሳስቀምጥ ለውይይት መነሻ ሐሳብ እንዲሆነን እንጂ አቋም በመውሰድ አይደለም። አስተውለው ከሆነ በጥያቄዎት ውስጥ ታላላቅ ሐሳቦችን አቅርበዋል። በሌሎች ታላላቅ የዓለም ሃይማኖቶች በወር አበባ ላይ ያለውን አስተያየት ነግረውናል። እስቲ ሌሎችም አከል ያድርጉበትና እኔም የአቅሜን ወደኋላ ላይ አከል አደርጋለሁ። እርሶንም ሆነ ሁላችንን የሚያስማማን አንድ ነጥብ ግን በአስተያየቴ ላይ እንደገለጥኩት፥ እንኳን በተፈጥሮ ግዳጅ ላይ ሆነን፥ በሌላውም ሁኔታ ውስጥ ሆነን እንኳ የማይለየን ቅዱስ አምላክ አለን። ሌሎችስ አስተያየታችሁ ምንድነው?

  ReplyDelete
 4. kesis ahun yerso dimidamee bewere abeba gize setoch ehotochachin mekureb yechilalu wesyes ayechilu weyem betekirstian megbat yechilalu ayechilum?

  ReplyDelete
 5. ወንድሜ ኤልያስ የአባቶችን መጽሐፍ እዚህ ላይ ያቀረብኩት፥ ኦርቶዶክሳውያን አበው መንፈሳዊ ሕይወታችንን እንዴት በብዙ አቅጣጫ እንደሚመለከቱት በማቅረብ እኛም እንድንወያይበት ነው። አስቸጋሪ የሆኑ ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ነገሮችን በሰከነና በረጋ መንፈስ መወያየትን እንድንለምድም ነው። ሆኖም የእኔን አስተያየት ቃል እንደገባሁት ብዙዎቻችሁ ከተወያያችሁ በኋላ አከል አደርጋለሁ። አንተም የመሰለህን ከአባቶችም የሰማኸውን ከቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትም ያነበብከውን አከል አድርግ። እንወያይበት። ስለአስተያየትህ በጣም አመሰግናለሁ። ከሁሉ በላይ በግልጥነት ለመወያየት ስምህን ስላስተዋወቅኸኝ በጣም አመስግናለሁ።

  ReplyDelete
 6. http://orthodoxinfo.com/praxis/menses.aspx I think it'll be best and a more honorable thing to do for you, father, if you could make a research on sensitive things like this before posting your own opinions. I love most of your blog posts and they seem scholarly. See what other Orthodox jurisdictions say about Menstruation, Emissions, and Holy Communion.

  ReplyDelete
 7. Thank you Michey. As you said in other post, this passage is from our church manuscript. If you want my opinion I will write in great detail.

  ReplyDelete
 8. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 9. (SORRY i did NOT notice my previous post had a grammatical error and here's the edited version) Yes Kesis you are right! But, we can NOT and should NOT use books such as Te'amrat and Dirsanats to base or justify our theological and/or canonical foundations. We can only use the Holy Scripture and patristic writings. All the canonical Orthodox Churches from Russia to Greek to Coptic reject the passage that you posted. There's NO problem if a woman enters a church when she has her menstrual cycle, as the church do NOT consider NATURE to be sin or unclean other radicalist (Pharisees of our time) see it. But WE cannot partake from the Holy Communion if we are bleeding-i.e. MEN or WOMEN. So to simply say God has allowed it seem more of a joke and belittles the significance of the Apostolic Church! After all why is the Church called Apostolic if she is NOT the sole preserver of the Apostolic cannon and Tradition??? Forgive me, Kesis, I, unworthy, am NOT trying to debate you...but I strongly believe such books in our church need academic reviews as they contradict(sometimes) the Apostolic teaching. With humility and love Mickey

  ReplyDelete