የሰዎችን ይሁኝታ ለማግኘት የምንጥረው እግዚአብሔር የሰጠንን ማንነት ስላላወቅነው ወይም ለመቀበል ስላቃተን ነው። በመሆኑም ከውስጣችን ያጣነውን ከሰዎች ለማግኘት እንጥራለን። ከሁሉ የሚያዛዝነው ግን እንዲያ ጥረን ግረን ያገኘነው ነገር ለእኛ እርካታ አለመስጠቱ ነው። ምክንያቱም ያ ከሰዎች ያገኘነው ማንነት፥ ሰዎች ስለ እኛነታችን የደረደሩት ቃላት ሁሉ ማንነታችንን ይሸፍነዋል እንጂ እንድናገኘው አያደርግም። ይህ ደግሞ እንደገና የሰዎችን ይሁኝታ ለማግኘት እንድንራብ ያደርገናል። እንዲህ ዓይነቱ ሕይወት ደግሞ ያደክማል።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን ባስተላለፈው መልእክቱ በምዕራፍ አንድ ላይ አጠንክሮ እንዳስቀመጠው በዓለም ላይ ክርስቶስን ለብሰን በድል አድራጊነት መመላለስ የምንችለው ሥፍራችንን ስናውቅ ነው። እግዚአብሔር አብ ዓለም ሳይፈጠር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ያዘጋጀልንን ሰማያዊ በረከት። በሰማያዊ ሥፍራ ተቀምጣችኋል፤ በሰማያዊ በረከት ተባርካችኋል ይለናል። ጠላት ዲያብሎስን የሚያስፈራው ማንነቱን ያወቀ ክርስቲያን ነው። . . .
No comments:
Post a Comment