Read in PDF
ባለፈው ትምህርታችን ስለ ጸሎተ ሃይማኖት መጻፍ ታሪካዊ ምክንያቱን አትተን ስለ እግዚአብሔር አንድነት ሦስትነት በመጠኑ አትተን ነው ያቆምነው። ዛሬ ከዚያ በመነሣት በምሥጢረ ሥላሴ ትምህርታችን ላይ ሊነሡ የሚችሉትን ጥያቄዎችና መልሶቻቸውን እናያለን። በጸሎተ ሃይማኖት ላይ ያሉትን ቃላትና ሐረጎች በመተንተን መንፈሳዊ ትርጉማቸውንም እናያለን።
1. ምሥጢረ ሥላሴ ማለት ምን ማለት ነው?
በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተማርነው መሠረት አንድ አምላክ በሦስት አካላት እንዳለ የምናምንበት የምንማርበት እውነት ነው።
2. ምሥጢረ ሥላሴ በሃይማኖት ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ ( የበቁ) ሰዎች የሚማሩት ነው?
አይደለም። እንዲያውም ገና ወደ ክርስትና የገቡ ሰዎች ሊማሩት የሚገባቸው ነገር ቢኖር አንዱ እግዚአብሔር በሦስትነት እንደተገለጠ ነው። ምሥጢረ ሥላሴ በፍልስፍና የምንማረው ሳይሆን በእምነት የምንቀበለው ስለሆነ። ዘዳግም 29፥29
3. የሥላሴ ትምህርት ለምን ምሥጢር ተባለ?
በኦርቶዶክሳውያን አባቶቻችን ዘንድ ምሥጢር የተባለው የሥላሴ ትምህርት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ እምነታችን ነው። ምሥጢር ሲባል የተደበቀ የተሰወረ ማለት ሳይሆን
• አንደኛ ራሱ እግዚአብሔር የሰው አእምሮ ተመራምሮ የማይደርስበት፤ 1 ጢሞቴዎስ 6፥16። ኢዮብ 11፥7_12፤
« እስመ እግዚአብሔር ኢይትረከብ በሕሊና እጓለ እመሕያው ወሕሊና እጓለ እመሕያው ኢይረክብ መለኮተ፤ ወህላዌ መለኮት ርኁቅ እምሕሊና እጓለ እመሕያው ወይትሌዐል ኵሎ ሕሊናተ ፈድፋደ። እግዚአብሔር በሰው ልጅ አስተሳሰብ ውስጥ አይገኝም። የሰው አስተሳሰብም መለኮትን ሊያገኝ አይችልም። የመለኮት አነዋወር (ሕላዌ መለኮት ከሰው ልጅ ሕሊና የራቀና ከህሊናት ሁሉ እጅግ ከፍ ያለ ነውና። ቴዎዶጦስ ዘእንቆራ
• ሁለተኛ፥ እግዚአብሔር ማንም በማይደርስበት ብርሃን ቢሆንም ራሱን ለፍጥረቱ ገልጦአል። መጀመሪያ ራሱን በፍጥረቱ በኩል ገልጦአል። መዝሙር 32፥6፤ ሐዋ 17፥24_28። ሮሜ 1፥20_21። በቃሉ ራሱን ገልጦአል። ቃሉን በባሪያዎቹ በኩል እየላከ እግዚአብሔር ማንነቱ በብዙ መንገድ ገልጦአል። 2 ጴጥሮስ 1፥21። መጨረሻም ራሱን በልጁ ገልጦአል። ዮሐ 1፥14፡18፤ ዕብራውያን 1፥1።
• ሦስተኛ፥ ወደዚህ ዕውቀትም ስንመጣ በዚህ ዕውቀት ለዘለዓለም ስለምንኖር ወደአምልኮ ይመራናል እንጂ አያስታብየንም። ምክንያቱም የምናመልከው አምላክ ሁል ጊዜ አዲስ ነውና። ሐዋርያም እንደተናገረው « ከእውቀት ከፍለን እናውቃለንና» የአምላካችንን ግርማውንና ጌትነቱን እያየን እናመሰግነዋለን።