Wednesday, March 31, 2010

የተመከረበት፥ የታደመበት፥ የተፈረደበት

በዚህች ዕለት የካህናት አለቆች በሸንጎአቸው ስለወሰኑት ውሳኔ ዮሐንስ በወንጌሉ እንዲህ ብሎ ነበር።

እንግዲህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ሸንጎ ሰብስበው። ምን እናድርግ? ይህ ሰው ብዙ ምልክቶች ያደርጋልና። እንዲሁ ብንተወው ሁሉ በእርሱ ያምናሉ፤ የሮሜም ሰዎች መጥተው አገራችንን ወገናችንንም ይወስዳሉ አሉ። በዚያችም ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረ ቀያፋ የሚሉት ከእነርሱ አንዱ። እናንተ ምንም አታውቁም፤ ሕዝቡም ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡም አላቸው። ይህንም የተናገረ ከራሱ አይደለም፥ ነገር ግን በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ነበረና ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ ሊሞት እንዳለው ትንቢት ተናገረ፤ ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም፥ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ። እንግዲህ ከዚያ ቀን ጀምረው ሊገድሉት ተማከሩ። ዮሐ 11፥47-53


የቀያፋ ንግግር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ እንደነገረን ከራሱ አልነበረም። አባቶቻችን በትርጓሜአቸው እንዳሉት << መንፈስ ቅዱስ አንደበቱን ከፍቶ አፉን ጸፍቶ>> አናገረው። የክርስቶስ ሞት ለቤዛነት የሚሆን ሞት እንደሆነ የነገረን ራሱ ቀያፋ ነበር፤ ሕዝቡ ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ቢጠፋ ይሻላል በማለት።
































1 comment:

  1. kale hiwot yasemalen kesis,enante america yalachihu memheranoch metshaf lemen atsfum?beteley yedogma metshaft ahunm etret alena bemenfesawi bekul gin nefsachewen yimarna pope shenoda bithu asawkewnal

    ReplyDelete