በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
እንኳን ለበዓለ ሆሣዕና አደረሳችሁ፤ እኔ ባለሁበት ቤተ ክርስቲያን በሎስ አንጀለስ ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዓሉ የተከበረው በታላቅ ድምቀት ነበር። ከሌላው ጊዜ አከባበር የዘንድሮውን ልዩ የሚያደርገው የሕፃናት ትምህርት ክፍል የአህያ ውርንጫ ማምጣቸው ነው። እንኳን ለሕጻናት ለዓዋቂዎች እንኳን ልዩ ደስታን ፈጥሮ ነበር። የሕጻን ነገር አትበሉብኝ እንጂ ትልቁ ልጄ በውርጫዋ መምጣት በጣም እንደተደሰተ ነግሮኛል።
በዛሬው ዕለት የስብከቴ ርዕስ የነበረው << በሮች ይከፈቱ የክብር ንጉሥ ይግባ>> በሚል ርዕስ ሲሆን መነሻ ጥቅሳችንም መዝ 23፥1-11 ያለው ነው። በትምህርቱ ላይ በዚህ ሳምንት በሚኖረኝ ብሎግ ለማብራራት እሞክራለሁ።
ይህ የመጀመሪያ ቀን የብሎግ ጽሑፌ ሲሆን እግዚአብሔር በፈቀደልኝ መጠን በአገልግሎቴ ያጋጠመኝን ለእናንተ ለማካፈል እሞክራለሁ። ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም ያድርሰን። አሜን ።
No comments:
Post a Comment