Saturday, April 3, 2010

በመስቀሉ ሰላምን አደረገ

እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። ቆላስይስ 1፥19

ምሥራቃውያን ኦርቶዶክሳውያን በሰሙነ ሕማማት የሚገኙት ን ቀናት ታላቁ ሰኞ፥ ታላቁ ማክሰኞ  (Great Monday, Great Tuesday ) እያሉ ይጠሩአቸዋል። በዚያ ልማድ የእኛም ቀዳሚት ሥዑር ታላቂቱ ቅዳሜ በመባል ትታወቃለች። በዚህ እለት አባቶቻችን መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞንን በዜማና በንባብ በመጸለይ፥ በቤተ ክርስቲያንና በክርስቶስ መካከል ያለውን ልዩ የሆነ ፍቅር በማሰብ ክርስቶስ የአዳምን ልጆች ሁሉ ከሲኦል ነጻ እንዳወጣ፥ በአካለ ነፍስ ወደሲኦል ወርዶ በዚያ ላሉት ነጻነትን እንደሰበከ ይናገራሉ፤ ያበሥራሉ፤ የኃጢአት የጥፋት ውሃ እንደጎደለ፥ ዓለም እንደዳነ ለማብሰር ቄጤማ ያድላሉ። ይህም ኖህ ከጥፋት ውሃ በዳነ ጊዜ ርግቡዋን ሲሰዳት ቄጤማ ይዛ መምጣትዋን የሚያመለክት ነው።

No comments:

Post a Comment