Friday, April 2, 2010

የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ

ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ
ወለትንሣኤከ ቅድስት ንሴብህ ኩልነ
ይእዜኒ ወዘልፈኒ

መምህራችን ሆይ ለመስቀልህ እንሰግዳለን
ቅድስት የምትሆን ትንሳኤህንም ሁላችን እናመሰግናለን
ዛሬም ዘወትርም

ዛሬ ቀኑን ሙሉ ስለ እኛ ኃጢአትና በደል የተሰቀለውን አምላክ ስናስብ ነበር። እንዴት የተባረከ ዕለት ነበር። አምላካችን ያደረገልንን አስደናቂ ውለታውን እንድናስተውል አባቶቻችንና እናቶቻችን ይህን ትውፊት ጠብቀው ስላስተላለፉልን ልናመሰግናቸው ይገባል። ክርስቶስ ኢየሱስ በዓይናችን ፊት ተስሎ እንዳይታይ ጠላት ዲያብሎስ አዚም እንዳያደርግብን የአምላካችን ውለታው ተስሎ በዓይናችን ፊት ሊታይ ይገባል። 

No comments:

Post a Comment