tag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post7518050045575562651..comments2023-05-18T06:05:53.642-07:00Comments on ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life): በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን? (ክፍል አንድ) ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life)http://www.blogger.com/profile/08292432464110136478noreply@blogger.comBlogger17125tag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-40044671344223663492013-01-11T22:29:47.671-08:002013-01-11T22:29:47.671-08:00ቀሲስ ለጥያቄየ መልስ ስለሰጡኝ አመሰግናለሁ፡፡ የጠቆሙኝንም መረጃዎች ተመልክቻለ...ቀሲስ ለጥያቄየ መልስ ስለሰጡኝ አመሰግናለሁ፡፡ የጠቆሙኝንም መረጃዎች ተመልክቻለሁ እንዲሁም ደግሞ የሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ የመጀመሪያ ካሴትም በፒያኖ የተቀመረ እንደነበረ ወንድሜ ነገረኝ በተጨማሪም በፒያኖ መጠቀም ማለት ልክ አሁን መናፍቃን እንደሚጠቀሙት ለእግዚአብሄር የተሰዋ እስከማይመስልና የአለም የአለም እንዲሸት ማድረግ አለመሆኑንም ነገረኝ ስለዚህም እርስዎንም ተጨማሪ ማብራሪያ የሰጠኝን ወንድምም አመሰግናለሁ እግዚአብሄር ይባርካችሁ ጸጋዉ ይብዛላችሁ እላለሁ፡፡Anonymousnoreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-47949220104153079612013-01-11T11:16:26.307-08:002013-01-11T11:16:26.307-08:00ወዳጄ ኤልያ ስ፥ግልጥ ስለሆነው ጥያቄዎችዎ በጣም አመሰግናለሁ። ነገር ግን ብዙ...ወዳጄ ኤልያ ስ፥ግልጥ ስለሆነው ጥያቄዎችዎ በጣም አመሰግናለሁ። ነገር ግን ብዙ ሐሳቦችን ስላስቀመጡ ሁሉን ለመዳሰስ ቦታ አይበቃንም። ሆኖም ግን ካነሡዋቸው አሳቦች መካከል፥

1. ቤተ ክርስቲያናችን በአስተምህሮዋ በኩል ችግር የለባትም የሚለው፥ እኔም የምስማማበት ይህ እውነተኛና ትክክለኛ አባባል ነው።
2. ባህላዊ ነው ስለሚሉት እስኪ ጥቀሱልን ስላሉት ፥ እርስዎ በዝርዝር የጠቀሱዋቸው ነገሮች በሙሉ ማለትም የሴቶች አገልግሎት፥ የሚበሉ የማይበሉ፥ አርጋኖን(ፒያኖ) የመሳሰሉት ነገሮች ላይ ያለን አስተያየት በአብዛኛው የተመሠረተው በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተሳሰባችን ሳይሆን በባህላችን ነው። አባቶቻችን ከአምስት መቶ አመት በፊት የወሰኑትን የገላውዴዎስ ውሳኔን ይመልከቱ።
3. እንደእነዚህ ዓይነቶቹን ነገሮች አንስቶ መወያየት ምእመናንን ለጥርጣሬ መስጠት ነው የሚለው አደገኛ አመለካከት ይመስለኛል። በተለይም በዚህ የመረጃ ዘመን መወያየትን ከሸሸን ምእመናችንን እሳልፈን የምንሰጠው በዕውቀት ላይ ላልተመሠረተ አይታ ነው። ባህል ሰፊ ነገር ነው። በግልጥ እለመወያየት፥ በእግቦ በሽሙጥ መናገር፥ ሐሜቱ፥ ጠልፎ መጣሉ ባህል ሲሆን ትውልድ ይገድላል። ስለሆነም አሁን እያደረግን ባለው ሁኔታ በግልጥ ሁሉን በመነጋገር መፍትሔ መስጠትይቻላል። ለተኩላ አሳልፍ የሚሰጠው፥ ተኩላውን አለማወቅ እንጂ አጥርቶ ማየት አይመስለኝም። ውይይትና መነጋገር አጥርቶ ማየትን ያመጣል። ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life)https://www.blogger.com/profile/08292432464110136478noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-80905448336914895742013-01-11T10:31:41.564-08:002013-01-11T10:31:41.564-08:00tsegawotin yabzalot kesis awo bergit yebetekirstia...tsegawotin yabzalot kesis awo bergit yebetekirstianachin chigr meweyayet melkam new neger gin wanaw kulf minchu maweki melikam new yehem be betekihent akababi ena yesinodosu siltan manes new yehem yemaygebachew hailoch gebitew silebetebetu new enji be astemirotua lay chigr yelewm mikiniatun eyandandu neger metsihaf kidusawein enji mahilawe hono ayemeslegni eski erso bahilawei yemilutin negerochi gili behone huneta giletsut yehen kebahil akuaya enji metsihaf kidusawei aydel yehen hig yewtaw ye ethiopia behal new yemibalutin eski giletsulin lelaw kononawens lishashal biasfelig siltanu yeman new ?miemanu weyes begroup yetederaje hail new liashashilew yekeyerlin yemilew ? Kesis andanid neger yemiawetut neger sewn wede tirtare yemewsid miemnaninim wedetesasate menged yemiamerachew new lemsale set lije silalet siltan bebetkirstian la ,sile mezimur mesaria argano (piano),yemibelu yemayebelu migbochin betemelet, sile endezih ayenet neger enweyay malet kiftet mefter new erso sinodos benezih neger lay yastelalefewn neger yawekalu biye egemitalew silezih yehenin lesinodosu entewew wanaw wengel eytekesin emenafkan weyem kenetaki tekula begochin madan yeshashal letekulaw bere kemekifet ahun yehe ayedelem yebetekirstian chig biye asbalew Anonymoushttps://www.blogger.com/profile/07701158835635276472noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-3543106775315840632013-01-11T10:26:45.305-08:002013-01-11T10:26:45.305-08:00የተከበሩ አስተያየት ሰጪዬ እግዚአብሔር ያክብርልኝ፤ የጠየቁኝን ጥያቄ ከመመለሴ ...የተከበሩ አስተያየት ሰጪዬ እግዚአብሔር ያክብርልኝ፤ የጠየቁኝን ጥያቄ ከመመለሴ በፊት እስኪ የተጠቀሰውን ጥቅስ በንባቡ አውድ እንየው። እንዲህ ይላል፥ « ባህል ማለት ሌማት ማለት ነው። ባህል ማለት ጻህል( ሳሕን) ማለት ነው። ምግቡ የሚቀመጥበት። ሌማቱን የሚሠራው ዘመኑ ነው። ቅዳሴው የሚተላለፍበት ፕሮጀክተር ሲተክል ፊልም ቤት አደረጉት የሚል ትውልድ፥ በአርጋኖን (በፒያኖ) ሲዘመር ደነሱበት የሚል ትውልድ፥ አድማሳቸው ሰፊ የነበረውን የቀደሙትን አባቶች ታሪክ በሚገባ ያላስተዋለ ትውልድ ብቻ ሳይሆን፥ ወንጌልንም በሚገባ ያልተገነዘበ ትውልድ ነው።» ስለሆነም ፒያኖም ሆነ ፕሮጀክተር የሚተላለፈውን ቃለ እግዚአብሔር ከሰው ልብ ለማድረስ መሣሪያ ናቸው እንጂ በራሳቸው መልእክት አይደሉም፤ እነርሱን የምናይበት አተያይ ግን ባህል ነው።

ይህን ካልኩ ግን ጥያቄዎ ወደተመሠረተበት ዋና ሐሳብ ልመለስ። ይኸውም አንድ ቤተ ክርስቲያን በፒያኖ መዘመር ትችላለች ወይ? ሁለት፥ በፒያኖ መዘመር የሚገባ ከሆነ ቤተ በፒያኖ መገልገልን ቤተ ክርስቲያን የምትቃወመው ለምንድነው? ከሁለተኛው ነጥብ ልነሣና፥ ቤተ ክርስቲያን በፒያኖ መዘመርን ተቃውማ አታውቅም። በዘመናዊቱ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ሰፊ ቦታ ያላቸውን ሦስት አባቶችን ልጥቀስ። አንደኛው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ናቸው። በጊዜው ይታይ የነበረውን የምዕራባውያንን ተጽዕኖ ለመግታትና ቤተ ክርስቲያኒቱ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንድትሰጥ ንጉሠ ነገሥቱና ፓትርያርኩ የበላይ ጠባቂዎች የነበሩበት ሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ የተማሪዎች ማኅበር ብዙዎች ሊቃውንትን እና ሊቃነ ጳጳሳትን በአባልነት ያቀፈና ያፈራ ሲሆን በፒያኖ ይጠቀም ነበር።

የዛሬው አቡነ መልከ ጼዴቅ የቀድሞው ሊቀ ሥልጣናት ሃብተ ማርያም ወርቅነህ በሚመሩት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ወጣት ሴቶችና ወንዶች በፒያኖ ከመዘመራቸው በላይ እስከ አቡነ ጳውሎስ ፕትርክና ድረስ (እርሳቸውም ለጥቂት ዓመታት ተጠቅመውበታል) እስመ ኃያል አንተ የሚለው በጊዜ ቍርባን የሚዘመረው የቤተ ክርስቲያናችን ዜማ በቅዳሴ ጊዜ በፒያኖ ይታጀብ ነበር። ይህ በአምስቱም ፓትርያርኮች ዘመን የተከናወነ ነው።

አሁን የማገለግልበት የድንግል ማርያም ካቴድራል ውስጥ የሚገኘው የሰንበት ትምህርት ቤት ስሙ ሃይማኖተ አበው ነው። ከሌሎች ሰንበት ትምህርት ቤቶች ልዩ የሚያደርገው ነገር ቢኖር፥ ፒያኖ ወንጀል ሆኖ በሚታይበት ዘመን መዝሙሩን የሚያጅበው በፒያኖ ነው። ይህን ሰንበት ትምህርት ቤት ሃይማኖተ አበው ብለው የሰየሙትና በፒያኖ እንዲዘመር ያደፋፈሩት፥ ቀደም ሲል ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲያገለግሉ የነበሩና፥ የሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር አባል የነበሩት አቡነ ጳውሎስ ናቸው።

የታሪክንና የሌሎችን ዝርዝር ማስረጃዎች http://www.ethiopianorthodox.org/amharic/miscellenous/betekirstianbefetena03.html ይመልከቱ።

በነገራችን ላይ ዛሬ ልጨኛ ( classic) ተብለው የሚታወቁት የቤተ ክርስቲያናችን መዝሙሮች እንደቸርነትህ፥ የአብርሃም አምላክ እና ሌሎችም ለፒያኖ ተብለው በኖታ ተቀምረው የተዘጋጁ መሆኑን ያውቃሉ? ይበቃናል። ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life)https://www.blogger.com/profile/08292432464110136478noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-75347878587722737742013-01-11T00:45:31.054-08:002013-01-11T00:45:31.054-08:00ቀሲስ እግዚአብሄር ይባርክዎት ትምህርቱ እራሳችንን እንድንመረምር የሚያደርግና ወ...ቀሲስ እግዚአብሄር ይባርክዎት ትምህርቱ እራሳችንን እንድንመረምር የሚያደርግና ወደ አንድነት የሚጠራ ነዉ፡፡ ግዜዎትን ካልተሻማሁ አንዲት ጥያቄ ብጠይቅዎት ደስ ይለኛል፣ ይህዉም እንደሚከተለዉ ነዉ በመልእክትዎ ዉስጥ ‹‹በአርጋኖን (በፒያኖ) ሲዘመር ደነሱበት የሚል ትውልድ›› የሚል አነበብኩ ቤተ ክርስቲያናችን በፒያኖ መዘመር ትችላለች ማለት ነዉ? እንዲህ ማድረግ የሚገባስ ከሆነ እስካሁን በፒያኖ መገልገልን የምትቃወመዉ ለምንድን ነዉ?Anonymousnoreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-24582307740766648632013-01-10T11:46:14.557-08:002013-01-10T11:46:14.557-08:00በረከት፥ ስለተሳትፎዎ በጣም አመሰግናለሁ። በዚህ አጋጣሚ ብሎጊቱን በማስተዋወቅ ...በረከት፥ ስለተሳትፎዎ በጣም አመሰግናለሁ። በዚህ አጋጣሚ ብሎጊቱን በማስተዋወቅ ደረጃ ያግዙን። ለሌሎች የድረገጽ ወዳጆችዎ በኢሜይል በፌስ ቡክ በትዊተር ያስተዋውቁአት። ይስደዱዋት። ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life)https://www.blogger.com/profile/08292432464110136478noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-17796971217193550982013-01-10T07:48:14.709-08:002013-01-10T07:48:14.709-08:00እግዚአብሔር ይስጥልን ቀሲስ። ይች ብሎግ በጣም ሳትስማማኝ አትቀርም። እስዎ በ...እግዚአብሔር ይስጥልን ቀሲስ። ይች ብሎግ በጣም ሳትስማማኝ አትቀርም። እስዎ በቀጥታ ለአስተያየቶች መልስ መስጠትዎ ደስ ይላል። ከላይ ለኔ በሰጡት አስተያየት እስማማለሁ። በርግጥም ይሄ ጠባብነት ምዕራባውያንንም እንዳጠቃ እርግጥ ነው። አጅሬ ሰይጣን ምን ይስራ፦ የመለያየትንና ከኔ ማን ይበልጣል የሚለውን ክፉ መንፈስ በሁሉም ውስጥ ለማስቀመት ይሞክራል። በረከትnoreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-75529470866848314102013-01-09T22:28:38.263-08:002013-01-09T22:28:38.263-08:00እርግጥ ነው፥ በዋናነት ልንነጋገር የሚገባን የእኛን አንድነት ነው። ሆኖም ግን ...እርግጥ ነው፥ በዋናነት ልንነጋገር የሚገባን የእኛን አንድነት ነው። ሆኖም ግን የእኛዋም ቤተ ክርስቲያን ብትሆን የዓለም አቀፍዋ ቤተ ክርስቲያን አካል ስለሆነች፥ በዓለም ደረጃ ስላለው ክርስትና መነጋገራችን አይቀርም። የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት World Church Council መሥራች አባል የሆነውም ለዚህ ነው። ዘመናዊው ኢኩሚኒዝም ሊመዘን የሚገባውም በምናየው የዲኖሚኔሽን ጥላቻና የበጎች ነጠቃ ሳይሆን በሊቀ ካህናቱ ጸሎት ነው። አንድ አድርገን በሚለው። ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life)https://www.blogger.com/profile/08292432464110136478noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-79082631197730390252013-01-09T22:24:42.091-08:002013-01-09T22:24:42.091-08:00ቀስቶ ወተረ ስምዎ ያስፈራል። አሜን ከማለትስ ውጪ ምን ይባላል? እንግዲህ ከምር...ቀስቶ ወተረ ስምዎ ያስፈራል። አሜን ከማለትስ ውጪ ምን ይባላል? እንግዲህ ከምርቃትዎ ጋር እጅዎ ከምን እያልን ስለሆነ፥ በተጻፉት ነገሮች ላይ አስተያየቶዎን በሰፊው ሰንዘር ያድርጉ። ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life)https://www.blogger.com/profile/08292432464110136478noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-1843816627778173292013-01-09T22:22:50.672-08:002013-01-09T22:22:50.672-08:00Thank you. Thank you. ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life)https://www.blogger.com/profile/08292432464110136478noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-33722539999242782262013-01-09T22:22:03.568-08:002013-01-09T22:22:03.568-08:00የተወደዱ አስተያየት ሰጪ በሚገባ እንዳቀመጡት፥ የዚህ የጡመራ መድረክ ዋና ዓላማ...የተወደዱ አስተያየት ሰጪ በሚገባ እንዳቀመጡት፥ የዚህ የጡመራ መድረክ ዋና ዓላማም በሰከነ መንፈስ ስለራሳችን በግልጽነት እንድንወያይ ነው። ወደዚህ የመነጋገር መንፈስ የሚያመጣንን አሳብ ሁላችንም ከየአቅጣጫው እንወርውር። ለዚህም አምላከ ቅዱሳን ይርዳን።
ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life)https://www.blogger.com/profile/08292432464110136478noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-53332218523414529772013-01-09T19:07:57.686-08:002013-01-09T19:07:57.686-08:00Endew Pentew kereto, yetekerew Orthodox ande behon...Endew Pentew kereto, yetekerew Orthodox ande behone. I don't care about Pente because that is not my faith. Let them care about themselves. The idea of ecumenicalism is not practical given the animosity that Penetes have against the Orthodox church.

Also, despite their delcared mission, the Western Pentes and the Catholics for that matter came to Ethiopia for other reasons other than the Gospel: 1) to spy Ethiopia for their governments, 2) to divide and weaken the Orthodox church and hence its government etc... Most of the Ethiopian emperors had wondered and asked why/how the missionaries skipped Libia, Egypt and Sudan and focused on Ethiopia if their mission were spreading the Gosple. The answer is obvoius. So, please let us focus on the Orthodox church; the Penete and Catholic chruches have their own leaders who care about their unity etc... Anonymousnoreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-31998226564264908212013-01-09T18:55:58.066-08:002013-01-09T18:55:58.066-08:00The analysis is fair and encouraging. Growing up, ...The analysis is fair and encouraging. Growing up, I also had lots of opportunities to see fist hand how the church is divided along tribal lines even before Weyane made it a policy. All your observations are correct in my opinion. Keep it up.... it is a very positive analysis that can help clean up some of the bad things around the church. Joro yalehe sima. Anonymousnoreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-3627071514596817622013-01-09T18:33:17.244-08:002013-01-09T18:33:17.244-08:00በመጀመሪያ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያን አንድነት በሚል ርዕስ ራሳ...በመጀመሪያ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የቤተክርስቲያን አንድነት በሚል ርዕስ ራሳችንን እንድንመረምር ስለፈቀደ ክብር እና ምስጋና ለእርሱ ይሁን። ቃለ ህይወት ያሰማልን ቀሲስ። በእውነት ይህ ጥያቄ ብዙ ሊያነጋግረን የሚችል ነው። ምክኒያቱም የራሳችንን ህይወት ቁጭ ብለን መመርመር እንደሚገባ ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እምነቷ እና አንድነቷ ምን ደረጃ ላይ ነው የሚለውንም እንደዚሁ በየጊዜው መመርመር ይገባል ብዬ አምናለሁ። እንደ እኔ አስተያየት በመጀመሪያ ጌታ መንፈስ ቅዱስ አይናችንን ከዘር: በከባህል እና ከስልጣን አንስተን በአንዱ በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ላይ እንድናደርግ አይናችንን ያብራ እላለሁ። ሌላው በዚሁ ፁሁፍ ላይ እንደሚለው የውስጥ መለወጥ ያስፈልጋልና ይህ ለውጥ ደግሞ የሚመጣው በእግዚአብሔር ቃል ነውና ከምንም በላይ ጊዜያችንን ቃሉን በማንበብ ልናጠፋ ይገባል። በመጨረሻ ቤተክርስቲያን; ካህናት አባቶችን እና ምዕመናንን ሰብስባ በዚህ ጉዳይ ላይ በመወያየት ያልገባው ጥያቄ በመጠየቅ እና በመረዳት: የሰማው ላልሰማው እያካፈለ: በአንድ መንገድ አና ዕምነት ለመጓዝ ከፍተኛ ጥረት ሊያደርግ ይገባል ብዬ አምናለሁ። እግዚአብሔር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተመሰገነ ይሁን። አሜን! Anonymousnoreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-30184159747261662112013-01-09T16:09:05.514-08:002013-01-09T16:09:05.514-08:00 ቀስቶ ወተረ እግዚአብሔር የመስገን አርሱ ሥራውን ሲጀመር አንዲህ ነው ከባጣገባ... ቀስቶ ወተረ እግዚአብሔር የመስገን አርሱ ሥራውን ሲጀመር አንዲህ ነው ከባጣገባቸው እያለ ሳናየው የኖርረነውን እንድናየው ያደርጋል ቀሲስ ማተዎስን ይመስል የሰውን ስምት የመነካት ተሰጦዎ በስከተዎ ብቻ ሳይሆን ወደ ጽሁፈዎም እየተጣበቀበዎ ነው ይበርቱ ማጠሩም ጥሩ ነው ግን እንዳይቋረጥ አደራ ይቀጥለ አንድገና እግዚአብሔር የቤተ ክረስቲያን ልሳን ስለ አደረገዎ ምሳጋናው ለርሱ ይሆን Anonymoushttps://www.blogger.com/profile/02313462305621675474noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-37317226689646184502013-01-09T16:04:25.457-08:002013-01-09T16:04:25.457-08:00የተወደዱ አስተያየት ሰጪዬ ይህ ችግር መጀመሪያ የመነጨው ከምዕራባውያን ወንድሞቻ...የተወደዱ አስተያየት ሰጪዬ ይህ ችግር መጀመሪያ የመነጨው ከምዕራባውያን ወንድሞቻችን እንደሆነ ከታሪክ ማስተዋል እንችላለን። ሚስዮናውያን ወደሀገራችን ሲመጡ ምድሪቱ ወንጌልን እንዳልሰማች ቆጠረው እንደሆነ ማስተዋል አለብን። በዚህ ጉዳይ ላይ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌና ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት የጻፉትን መጣጥፎች The Missionary Factor in Ethiopia (Studien Zur Interkulturellen Geschichte Des Christentums) ማየት ይችላሉ። እውነተኛ የሆነ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት በኢኩሜኒዝም መንፈስ ለመወያየት ብዙ በሮች ይኖራሉ ብዬ አምናለሁ። ይህም ከሁሉም ወገን ሲሆን ነው። ስለዚህ ጉዳይ በሦስተኛው የቤተ ክርስቲያን ባሕርይ ላይ እንመለሳለን። ይቆየን።ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ( The Orthodox Life)https://www.blogger.com/profile/08292432464110136478noreply@blogger.comtag:blogger.com,1999:blog-8474200614194328478.post-10229020162656170982013-01-09T15:42:51.950-08:002013-01-09T15:42:51.950-08:00እግዚአብሔር ይስጥልን ቀሲስ፦ በጣም ደስ የሚል እይታ ነው። እግዚአብሔር ጸጋው...እግዚአብሔር ይስጥልን ቀሲስ፦ በጣም ደስ የሚል እይታ ነው። እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልዎት እያልሁ የሚከተለውን አስተያየት ብሰነዝርስ፦ መቼም ኦርቶዶክሳውያንን ከሚያጠቃን ነገር አንዱ ጠባብነት ነው። አንዲት ሃይማኖት ማለት ኦርቶዶክስ ናት እየተባልን አድገን አዕምሮአችን አለማቀፋዊ የሆነ እይታን ማየት ተስኖታል። በክርስቶስ የሚያምን የሌላ ዲኖሚኔሽን አማኝ የአንዲቷ ቤተ ክርስቲያን አባል የሆነ አይመስለንም። አንዲት ቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክስ ወይም ጴንጤ ሳይሆን በክርስቶስ ያሉ ሁሉም ናቸው። ይህንን በድፍረት መቼ ይሆን መናገር የምንጀምረው። በሚቀጥለው ጽሁፈዎት ላይ ይህንን ሰፋ አድርገው የበለጠ ዓለማቀፋዊ ቢያደርጉትስ? በረከትnoreply@blogger.com